ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች ቢኖሯትም በባሕር በር እጦት የዓለምን የባሕር ንግድ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ መቀላቀል አለመቻሏ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች እያጋለጣት መሆኑን የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል ገለጹ።
የባሕር በር ጥያቄ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ጥያቄ መሆኑንም አንስተው፤ ሕዝቡ በዘር፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ሳይከፋፈል በባሕር በር ጥያቄ ዙሪያ በአንድነት መቆም እንዳለበት አመላክተዋል።
“ቀይ ባሕርን ያጣንበት መንገድ ሕጋዊ ነው ወይስ ተፅዕኖ ነበረበት? በዚያ ሂደት ከመጋረጃ ጀርባ የሌሎች አካላት ሚና ምን ነበር?” የሚለውንም ማጤን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የባሕር በር ጥያቄ አሁን መነሳቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባሻገር ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ጭምር በእጅጉ አስፈላጊ ስለመሆኑም ነው የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል የተናገሩት።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebcdotstream #ethiopia #seaport #redsea