ሁሉም ዜጋ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዘብ መቆም አለበት ሲሉ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህሩ አቶ ሙሉዓለም ኃ/ማሪያም ገለጹ።
አቶ ሙሉዓለም ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በተለያዩ ጊዜያት የምታከናውናቸው ተግባራት እንዳሉ አንስተዋል።
አክለውም፥ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ያነሳችው የባሕር በር ጥያቄ የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ሁሉም ዜጋ በአንድነት መቆም እንዳለበት አመላክተዋል።
በሜሮን ንብረት
#ebcdotstream #ethiopia #seaport #nationalinterest