Search

የሳይበር ደኅንነት የሁሉንም የጋራ ጥረት የሚፈልግ ሥራ ነው - የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ

ሓሙስ ጥቅምት 06, 2018 93

6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር "የሳይበር ደኅንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ሀሳብ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ፤ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚተገብሯቸውን የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች የሳይበር ደኅንነት በማስጠበቅ ረገድ በጋራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
 
ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ በማውጣት እንዲሁም በዘርፉ ብቁ የሠው ሃይል በማፍራት የተለያዩ ሥራዎችም እየተሠሩ እንደሚገኝም አንስተዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በበኩላቸው፤ ቴክኖሎጂዎችን እና መሰረተ ልማቶችን ከምንጊዜውን በላይ ከሳይበር ጥቃት መጠበቅ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
የሳይበር ደኅንነት ወር በጉዳዩ ላይ የማኅበረሰቡን ብሎም የተቋማትን ሠራተኞች እና አመራሮችን ንቃተ ህሊና በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም ገልፀዋል።
 
በሳሙኤል ወርቃየሁ