የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የተበረከተለት የእውቅና ሽልማት የፋኦ መርሐ ግብሮችን በብቃት በመተግበር በተለይም ዘላቂ የግብርና እና የገጠር ልማትን፣ የምግብ ዋስትናን እና ፈጠራን ለማሳደግ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈጻሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በጣሊያን ሮም በሚገኘው የፋኦ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ከድርጅቱ የተበረከተውን ዓለም አቀፉን የስኬታማ ተቋም ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት በጣሊያን ሮም ባካሄደው የዓለም የምግብ ጉባኤ ላይ ለኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ምርጥ የዘላቂ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀም በሚል ዘርፍ ዕወቅና መስጠቱ ይታወሳል፡፡
#ebc #ebcdotstream #ethiopia #Agriculture #fao