ከታማኝ ግብር ከፋዮች የሚሰበሰበው ገቢ አዲስ አበባን ለንግድ እና ለመኖር የተመቸች እና በአለም አቀፍ ደረጃም ተመራጭና ተወዳዳሪ እያደረጋት ይገኛል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና መርሐ ግብር አካሂዷል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት፤ ዛሬ የከተማችንን ታማኝ ግብር ከፋዮች በታላቅ ድምቀት ሸልመናል፤ ተሸላሚ ግብር ከፋዮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ከታማኝ ግብር ከፋዮች በምትሰበስበዉ ገቢ በከተማዋ በአስደናቂ ሁኔታ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት፣ የተማሪዎች ምገባ እና ሌሎች የህዝቡን የኑሮ ጫና ያቀለሉ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡
ይህም ከተማዋን ለንግድ እና ለመኖር የተመቸች እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃም ተመራጭና ተወዳዳሪ እያደረጋት እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ይህ ለዉጥ ለግብር ከፋዮች ተጨማሪ አሴት፣ ለቢዝነስ ማህበረሰቡ ተጨማሪ የሀብት መፍጠሪያ ምንጭ ነዉ ሲሉም ጠቅሰዋል።
በቀጣይ በግብር አሰባሰብ ዙሪያ የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ዲጂታላይዝ በማድረግ፣ በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈንና ክፍተቶችን በመሙላት የሁለንተናዊ ብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማን እንገነባለን ብለዋል።
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #AddisAbaba #Tax