Search

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከፍተኛውን ዕድገት ታስመዘግባለች - አይኤምኤፍ

ዓርብ ጥቅምት 07, 2018 168

ኢትዮጵያ .. 2025 ከሰሀራ በታች ከሚገኙ ከፍተኛ ዕድገት አስመዝጋቢ ሀገራት መካከል አንዷ እንደምትሆን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትንበያ አመላከተ።

ከሰሀራ በታች ከሚገኙ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 7.2 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሆኗም ነው በሪፖርቱ የተመላከተው።

ኢትዮጵያ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እውን በማድረግ እና አዳዲስ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማሳለጥ ላይ መሆኗ፤ ይህን ዕድገት እንደምታሳካው ማሳያ ይሆናል።

ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ መንግሥት የጀመራቸው ውጥኖች ከከተማ እስከ ገጠር መተግበር መጀመራቸውም ቀጣይነት ያለው ዕድገት የምታስመዘግብ ሀገር መሆኗን የሚያመላክት ነው።

ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ይገለጻል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) .. 2025 ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራትን የዕድገት ትንበያ ባወጣበት ሪፖርት እንዳለው፣ ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎች ሳይበግሩት የቀጣናው ዕድገት ግስጋሴውን ቀጥሏል።

እንደ ተቋሙ መረጃ ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በፈረንጆቹ 2024 ከነበራቸው 3.5 በመቶ አማካይ ዕድገት 2025 ወደ 3.8 ከፍ እንደሚሉም ተመላክቷል።

ይህ ቁጥር .. 2026-2027 ወደ 4.4 በመቶ ከፍ እንደሚልም ነው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያስታወቀው።

በሰለሞን ከበደ

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #growth #SSA #IMF