ኢትዮጵያ የጀመረችው የዕድገት መንገድ እንዳይሳካ የሚያደርጉ የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቿን ጫና ለመመከት የውስጥ አንድነቷን ማጠናከር አለባት ሲሉ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዳለ ንጉሴ ገለጹ።
ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ምዕራፎች እያሳኳቸው ያሉ ፕሮጀክቶች ታሪክን የመድገም እና ስልጣኔን የማስቀጠል ባህልን የሚያሳድጉ ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንዳታንሰራራ የሚደረግ የውጭ ጠላቶች ጫና እና የእጅ አዙር ቀኝ አገዛዝን በአንድነት ቆሞ በመመከት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እንደተገነባው ሁሉ በተመሳሳይ አካሄድ የባሕር በር ተጠቃሚነትን ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል።

በተለያየ መልኩ ሲደረግባት የነበረውን ጫና ተቋቁማ አልፋ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን እውን ያደረገችው ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለማሳካት መሥራቷን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
መንግሥት በቅርቡ ይፋ ያደረጋቸውን ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ከዳር ለማድረስ የሕዝቡ አንድነት ወሳኝ በመሆኑ፤ መላው ኢትዮጵያውያን ይህን ታሳቢ በማድረግ በአንድነት መቆም እንዳለባቸው አመላክተዋል።
በሄለን ተስፋዬ
#ebcdotstream #ethiopia #unity #GERD #seaport