Search

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አይኤምኤፍ በአባል ሀገራት ድርሻ ላይ ያደረገው ማሻሻያ በፍጥነት እንዲተገበር ጠየቀ

ዓርብ ጥቅምት 07, 2018 60

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአባል ሀገራት ድርሻ ላይ ያደረገው ማሻሻያ በፍጥነት እንዲተገበር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (/) ጠይቀዋል።

/ር ኢዮብ ከአይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን በተደረገ ውይይት ወቅት እንዳሉት፤ እየታዩ ያሉ ዕድገቶችን ወቅታዊ እና ፍትሐዊ በሆነ የድርሻ ማሻሻያ ማጠናከሩ የወቅቱን የዓለም ኢኮኖሚ ገጽታ በተሻለ ሁኔታ ያንፀባርቃል ብለዋል።

አይኤምኤፍ 50 በመቶ የድርሻ ማሻሻያ ጭማሪ ማድረጉ፤ የፋይናንስ ዘርፉን ሴፍቲ ኔት እና የአባል ሀገራትን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት አንድ እርምጃ የሚያሻግር መሆኑንም አንስተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው፥የድርሻ ጭማሪውን እና ፈጣን ማሻሻያውን ብንቀበልም፤ የድርሻ ማስተካከያው በአስቸኳይ ይተግበር መባሉ የተጋነነ አይደለምብለዋል። 

ኢትዮጵያን ጨምሮ ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት አይኤምኤፍ አጋር መሆኑን አንስተው፤ ተከታታይ የድርሻ ማስተካከያዎች መዘግየታቸው እነዚህ ሀገራት ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዳያገኙ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

አሁን ላይ በማደግ ላይ ያሉ አባል ሀገራትን ድርሻ ለመጠበቅ የተጀመረውን መንገድም አድንቀው፤ በማዕቀፉ ውስጥ ያለውን ዝቅተኛ ውክልና ማስተካከል እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

ሚዛናዊ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት፤ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ተገቢው ውክልና ላልተሰጣቸው ሀገራት ወደፊት በሚደረጉ የድርሻ ማስተካከያዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባልብለዋል።

በሰለሞን ከበደ

#ebcdotstream #ethiopia #imf