የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ከአላስካው የሰላም ውይይት በኋላ በሀንጋሪ በድጋሚ ሊገናኙ መሆኑ ተሰምቷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በውይይታቸውም ሁለቱ መሪዎች በቡዳፔስት በአካል ለመገናኘት መስማማታቸውን ተናግረዋል።
በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት ለመገናኘት ቀጠሮ የያዙት መሪዎቹ፤ መቋጫ ባላገኘውን የሩስያ - ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ከስምምነት ለመድረስ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከአሜሪካ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማግኘት እና በጦርነቱ ዙሪያ ለመወያየት ዛሬ አሜሪካ የሚገቡ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ውይይታችን ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረገው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ላይ ያተኩራል ብለዋል ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#ebcdotstream #USA #Russia #Trump #Putin