Search

7ቱ የጉባ ብስራቶች - የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚያጎለብቱ ተደማሪ አቅሞች

ዓርብ ጥቅምት 07, 2018 116

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክቶችን ነድፋ እየሰራች ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ 30 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ የምትተገብራቸውን 7 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
7ቱ የጉባ ብስራቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የኢኮኖሚ አቅም እንደሚያጠናክሩም የተለያዩ ምሁራን ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ መምህር የሆኑት ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር)፤ የኒውክሌር ፕሮጀክቱ እና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች ሀገሪቱ በኃይል አቅርቦት ያላትን አቅም ከማሳደግ በዘለለ ኢንቨስትመንት የመሳብ እና የውጭ ምንዛሬን ከማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምራ እየጨረሰች መሆኑን በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማሳየቷን በመጥቀስ፣ በቀጣይም ሜጋ ፕሮጀክቶቹን ማጠናቀቅ እንደምትችል መገመት አይከብድም ብለዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት አቶ ጌታቸው ታደሰ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የቤት ልማት እና ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ መሰረተ ልማቶችን ከማስፋፋት፣ የሥራ እድልን ከመፍጠር እና የዜጎችን ገቢ ከማሻሻል አኳያ ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ 7ቱ የጉባ ብስራቶች የሀገሪቱን ድኅነት በመቀነስ የዜጎችን አኗኗር ከመቀየር አንፃርም ሰፊ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል።
 
በሜሮን ንብረት