Search

የኢትዮጵያ ሁለቱ ፈተናዎች - ከትናንት እስከ ዛሬ

እሑድ ጥቅምት 09, 2018 48

ኢትዮጵያ በታሪክ ጉዞዋ፣ የባዳና የባንዳ ሴራ ያልፈተናት ወቅት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ከጥንት ጀምሮ ከዳተኞች እና የውጭ ጠላቶች ተባብረው ሀገርን ለማፍረስ ያሴሩበት አጋጣሚ ለቁጥር የሚታክት የኢትዮጵያ ታሪክ አካል ሆኗል።

በእርግጥ እንዲህ ያለው በሽታ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ ገባ ቢባል ብዙ ዘመናትን ወደኋላ መቁጠር የሚያስችል ቢሆንም በጣሊያን ወረራ ወቅት ግን እንዲህ ያለው ፈተና ከወረራው እኩል ኢትዮጵያን እንደፈተናት ማስታወስ ይቻላል።

በዚህ ወቅት ሀገራቸውን ከድተው ከወራሪዎች ጋር ያበሩ፣ መረጃ ያቀበሉ እና ወገኖቻቸውን የወጉ ባንዳዎች መከሰታቸውን ታሪክ ያስረዳል።

መልኩ ይለያይ እንጂ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም እና ምስጢር ለጠላት አሳልፎ በመስጠት በየፊናቸው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለሙ አልሳካ ቢላቸው እንጂ ብዙ ጥረዋል፣ ደም አፍስሰዋል።

በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ ለዘመናት ያንቀላፋችበትን የጨለማ ዘመን በብርሃን ለመቀየር ስትነሳ እንዲህ ያለው ፈተና ጎልብቶ ይመጣባታል።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጀመር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችን በመቀስቀስ፣ ፕሮጀክቱ እንዳይሳካ የሰሩ ባዕዳንም ሆኑ ተላላኪዎቻቸው ጥቂት እንዳልነበሩ ሲታሰብ ነው።

እዚህ ላይ ይበልጥ የሚገርመው ግድቡ ግንባታው ሲጀመር የነበረው መከራ እና ስቃይ ወደኋላ ላይ ረገብ ብሎ ታይቷል። ምክንያቱ ደግሞ ፕሮጀክቱ የትም እንደማይደርስ እርግጠኞች የሆነበት ወቅት ስለነበር ነው።

ይህን ፕሮጀክት ከሞተበት አስነስቶ ለፍጻሜ ለማድረስ 2011 . ጥረቶች ሲጀመሩ ደግሞ ከሀገር ቤት እስከ ዓለም አቀፍ የደረሱ የባንዳ እና የባዳ ጥምረቶች በየጎራቸው ተሰባስበው የሀገርን ልማት ለማደናቀፍ እንደጣሩ ተስተውሏል።

እንዲህ ያለው ጥረት የሚጎላው ታዲያ ኢትዮጵያ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ስትጀምር ነው፤ ያኔ የበሉበትን ወጨት ሰባሪዎች ያሳደጋቸውን ሕዝብ መልሰው ይኮረኩማሉ፤ ልማት እንዳይስፋፋ ይጥራሉ።

ስለሀገራዊ አጀንዳ የወደብ ባለቤትነት ጉዳይም ሆነ ስለልማት ሲነሳ አንዳንድ በዳያስፖራው ውስጥ የመሸጉ እና ሀገር ውስጥ የሚገኙ ሃሳዊዎች የነገር ሾተላቸውን ይመዝዛሉ።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ድል ያደረገችበት ሁሉ ባንዳ እና ባዳ ጥምረት ፈጥረው የገጠሟት ቢሆንም ሁሉንም በድል መወጣት ችላለች።

የገጠማትን መከራ ሁሉ ማለፍ የምትችለው ኢትዮጵያ፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይም ይህንኑ የገጠማትን ፈተና በማለፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቿን በስኬት እያስፈፀመች ቀጥላለች።

በተለይ በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ እየታየ ያለው ውጤት ለባንዳና ለባዳዎች የእራስ ምታት ቢሆንም ተጠናክሮ የሚቀጥል እንጂ የሚቆም አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) መግለፃቸውም አይዘነጋም።

ባዳ እና ባንዳ ሊያጥላላቸው የሚሞክሩ ፕሮጀክቶችም ከሀገርም አልፈው ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር ተሞክሮ እየሆኑ ነው።

ዓለምም በትብብር ማዕቀፍ የተቃኙት የኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች ብሩህ ጊዜ የሚያመላክቱ መሆናቸውን እየመሰከረም ይገኛል።