Search

በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይልን ተግባራዊ ማድረግ ለሁለንተናዊ ዕድገት መሰረት የሚፈጥር ነው - ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር)

እሑድ ጥቅምት 09, 2018 71

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ተግባራዊ ስታደርግ ሁሉንም ዘርፎች ማሳደግ የሚችል አቅም ይፈጠራል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ኃይል ፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኒውክሌር ኃይል መገንባትና ሥራ ላይ ማዋል በጤና፣ በግብርና፣በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን እና መሰል ዘርፎች ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነውም ብለዋል።
ዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ ከኢቲቪ አመሻሽ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል የኒውክሌር ኃይል ግንባታ እውን ስታደርግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቁመናችንን ለመጨመር ይረዳናልም ነው ያሉት።
የኒውክሌር ኃይል በዓለማችን ለሰላማዊ ግልጋሎቶች ዉሏል የሚሉት ጥላሁን ተስፋዬ (ዶ/ር) ኢትዮጵያም የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጄንሲ መስራችና አባል በመሆኗ አካሄዱን በተመለከተ ድጋፍ የምታገኝበት አግባብ ስለመኖሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይልን ለውስን ዓላማዎች በአይሶቶፕ፣ በግብርና እና መሰል ዘርፎች ተግባራዊ ስታደርግ መቆየቷንም አስታውሰው፤ አዲስ ይፋ የተደረገው የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም ሀገራዊና ሰላማዊ ዓለማዎችን ያነገበ እንዳሆነም ገልጸዋል።
የኒውክሌር ኃይል ግንባታ ሲጠናቀቅ በውኃ ኃይል ማመንጫዎች ላይ የተመሰረተውን የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት ጥገኝነት በማላቀቅ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋልም ነው ያሉት።
 
በመሀመድ ፊጣሞ