Search

የባሌ ዞን ልማት አዲስ ተስፋና ጉልበት የተፈጠረበት ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ማክሰኞ ጥቅምት 11, 2018 38

የባሌ ዞን ልማት ለአካባቢው ኅብረተሰብ አዲስ ተስፋና ጉልበት የተፈጠረበት ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።
በባሌ ዞን የታየው ልማት የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬ መሆኑን ያሳየ እንደሆነው ጠቁመው፤ የባሌ ዞን በአጭር ጊዜ ተለውጦ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።
የባሌ አካባቢ ባለመልማቱ ቁጭት እንደነበር አንስተው፤ አሁን ላይ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በከተማ ልማት ሰፋፊ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንና ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እንደሚሆን አንስተዋል፡፡
የባሌ አካባቢ የተረሳ እና የተደበቀ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሽመልስ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቁርጠኝነት አካባቢው እንዲቀየር በማድረጋቸው ምስጋና አቅርበዋል።
በባሌ የተሰራው ልማት ለሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ትልቅ መሰረት የሚጥል እና በቀጣይ ለሚሰሩ ሥራዎች ጉልበት የሚሆን ነው ብለዋል።