Search

በኢትዮጵያ የተጀመሩ ስራዎችን አለማድነቅ ንፉግነት ነው - አቶ ጁነዲን ሳዶ

ማክሰኞ ጥቅምት 11, 2018 41

በኢትዮጵያ የተጀመሩ ስራዎችን አለማድነቅ ንፉግነት ነው ሲሉ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጁነዲን ሳዶ ተናገሩ፡፡

እኛ በእድሜ ከእርሶ በፊት ሆነን በመላ ሀገሪቱ ስንዞር ያላየነውን ነገር የማየት አቅም በመፍጠሮ ላመሰግኖ እወዳለሁ ሲሉም አቶ ጁነዲን ሳዶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

የተጀመረውን ነገር ሳያደንቁ ሌላ ነገር ማሰብ ንፉግነት መሆኑን አንስተው፤ መንግስት ለመጪው ትውልድ ውበትን ብቻ ሳይሆን ያለውን ሀብት ገልጦ ማሳየቱ ትልቅ ነገር መሆኑን ገልፀዋል።

የባሌን የተፈጥሮ ሀብት አስመልክቶ የተሰሩ ጥናቶች ከዚህ ቀደም እምብዛም ነበሩ ያሉት አቶ ጁነዲን፤ የሶፎ ዑመር ፕሮጀክት የባለሙያውን፣ የአመራሩን፣ የሀገሪቱን እና የህዝብን አይን ለተሻለ ጥናት እና ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከዳሎል በረሃ አንስቶ እስከ ሰነቴ አናት ድረስ ሁሉም ነገር ያላት ባለፀጋ ሀገር መሆኗንም አቶ ጁነዲን ሳዶ አንስተዋል።

ዛሬ ላይ ሀገሪቷ በማዕድን፣ በእርሻ፣ በልማት፣ በቱሪዝም እና በመሰረተ-ልማት የተሟላች ናት ያሉት አቶ ጁነዲን፤ የማደግ እድላችን በእጃችን ላይ ነው ብለዋል።

ህዝቡም በትብብር አንድ መስመር እየያዘ በመሆኑ ልማትን ማምጣት እና ድህነትን ማስወገድ ይቻላል ነው ያሉት።

በሴራን ታደሰ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #bale #sofomer