የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት ተገናኝተው ለመወያየት ዕቅድ እንደነበራቸው ይታወቃል።
ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከፑቲን ጋር ያደረጉትን የስልክ ውይይት ተከትሎ ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጡ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው የተመሩ የከፍተኛ አማካሪዎች ቡድኖች ተገናኝተው በሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት የሚካሄደውን የመሪዎች ውይይት እንደሚያዘጋጁ ተናግረው ነበር።
ሆኖም የዋይት ሀውስ ባለስልጣን ለሲ.ኤን.ኤን እንደተናገሩት፥ በማርኮ ሩቢዮ እና በሰርጌይ ላቭሮቭ በሚመሩ ቡድኖች መካከል ይካሄዳል ተብሎ የተጠበቀው ውይይት ለጊዜው ተሰርዟል።
ሆኖም እስከአሁን ለውይይቱ መሰረዝ የተሰጠ ምንም ዓይነት ይፋዊ ምክንያት የለም።
በትራምፕ እና በፑቲን መካከል የተካሄደው የመጨረሻው ውይይት ከ2 ወራት በፊት በአላስካ፣ አንኮሬጅ የተካሄደው መሆኑ ይታወቃል።
በሴራን ታደሰ
#ebcdotstream #Trump #Putin