Search

የነገዋ ኢትዮጵያ ከዛሬዋ በላይ ቆንጆ ትሆናለች - ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል

ማክሰኞ ጥቅምት 11, 2018 78

በባሌ ያየናቸው ውብ የተፈጥሮ መስህቦች የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንዴት እየተሠራች እንዳለች እና የነገዋ ኢትየጵያ ደግሞ ምን ያህል ቆንጆ እንደምትሆን ያየንበት ነው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ።

ወይዘሮ ሙፈሪያት ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ባደረጉት “የሶፍ ኡመር ወግ” ውይይት ላይ ነው።

እዚህ ቦታ በመገኘቴ ሁለት ዓይነት ስሜት ተሰምቶኛል ያሉት ሚኒስትሯ፤ የመጀመሪያው፥ “ይህን ሁሉ ሀብት ይዘን እንዴት ደሃ ሆንን፣ መርጠን ወይንስ ወስነን? የሚል ቁጭት” መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሁለተኛው ደግሞ፥ በአጭር ጊዜ በተከናወኑ ሥራዎች ይህን ያህል ለውጥ ከመጣ፤ ተጨማሪ ጊዜ ወስደን ብንሠራ ምን ያህል ልናድግ እንደምንችል ሳስበው ተስፋ ይሰማኛል ብለዋል።

የባሌ ጉብኝታችን ወደ ኢኮኖሚያው ጥቅም መቀየር የሚችሉ የኢትዮጵያ ሀብቶች ምንድናቸው፣ የት ይገኛሉ? የሚለውን ለይቶ ሲያበቃ ፕሮጀክቶችን አቅዶ የመፈጸም፣ ጀምሮ የመጨረስ የላቀ የአመራር ጥበብ ያየንበት እና የተማርንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል። 

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#ebcdotstream #ethiopia #bale #sofumar #AbiyAhmedAli