የወል ትርክት ሁሉም ዜጋ አቅም የሚያዋጣበት እና ነባር ስብራትን በጋራ የሚሸከምበት አካሄድ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጹ።
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ባደረጉት “የሶፍ ኡመር ወግ” ውይይት ላይ ነው።
የጋራ ትርክት ካመጣቸው ስኬቶች አንዱ ሕዳሴ ግድብ ነው ያሉት ዲያቆን ዳንኤል፤ ሕዳሴ የዘገየ ትርክት ነው ከሚለው አስተሳሰብ ወጥተን ተጨባጭ ድል አግኝተናል ብለዋል።
ሀገር በወል ትርክት ትፈርሳለችም፣ ትገነባለችምና፤ የሀገር ብሔራዊ ጥቅም የሚረጋገጠው በጋራ የወል ትርክት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በወል ትርክት የምንተባበረው ለምንድነው ብለን ራሳችንን መጠየቅ እንዳለብን ጠቁመው፤ የወል ትርክት በተናጠል የማይደፈረውን በተደመረ ክንድ ለማሳካት የሚያስችል ስለመሆኑ አስረድተዋል።
የፍልስፍና መምህሩ እንዳለ አበራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የወል ትርክት በጋራ ጉዳይ ዙሪያ ስለሚያጠነጥን፤ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አለው ብለዋል።
ያለመግባባትን በማስወገድ ህብረተሰቡን ለአንድ ዓላማ የሚያሰልፈውን የጋራ ትርክት መገንባት ለነገ የሚባል አይደለም ነው ያሉት።
በሴራን ታደሰ
#ebcdotstream #ethiopia #thecommonnarrative #የወልትርክት