Search

የኢትዮጵያ ጠላቶች በሀገሪቱ ውድቀት ሀገር ለመገንባት የሚሞክሩ ናቸው

ረቡዕ ጥቅምት 12, 2018 61

ኢትዮጵያ እስካሁን ባለፈችባቸው ዘመናት ወዳጅም ጠላትም ያፈራችባቸው ብዙ ሀብቶች እንዳሏት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዳለ ንጉሴ ይገልጻሉ፡፡
የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን ጠላቶች በሁለት ከፈለው አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ዋነኞቹ ጠላቶች በሀገሪቱ ውድቀት ላይ ሀገር ለመገንባት የሚሞክሩ እና የራሳቸውን የቤትሥራ መስራት ያልቻሉት ናቸው ብለዋል።
ሌለኞቹ ደግሞ ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛትን አስተሳሰብ እንዳናስቀጥል አድርጋናለች ብለው የሚፃረሯት መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ይህንን መነሻ አድርገው ሀገሪቱን አንገት ለማስደፋት በእያንዳንዱ ፖሊሲያቸው ውስጥ በማካተት ታትረው የሚሰሩ ስለመኖራቸው ነው ያነሱት።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በቀጥታ ከሚያደርጉት ጫና ባሻገር የእጅ አዙር ጣልቃ ገብነቱም አያሌ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ያላት ብዝኀ ሃይማኖት እና ባህል የእድገቷ እና የጉልበቷ ምንጭ እንዳይሆን ባዳ እና ባንዳዎች ሲተባበሩ መቆየታቸውን አውስተዋል።
ይህንን ጫና ተቋቁማ ሕዳሴን የገነባችው ኢትዮጵያ፣ አሁንም ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ዘርፈ ብዙ ሥራ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።
በሴራን ታደሰ