የዲጂታላይዜሽን መስፋፋትን ተከትሎ በተለያዩ ጊዜያት የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ ዓለማት ይከሰታሉ።
በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃቶችን ከመከላከል ባለፈ ጠንካራ የተቋማት የሳይበር ደህንነት ስርዓትን ለመፍጠር በየጊዜው የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።
ሀገራዊ የዲጂታል ሽግግርን ለማረጋገጥ የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ስርዓት ማጠናከር እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር መከላከል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሀመድ ፈረጃ ገልጸዋል።
የሳይበር ጥቃት ሊያደርስ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና መከላከል የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚገባም አንስተዋል።
የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያና የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማኅበር መስራች የሆኑት ብርሃኑ በየነ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያመጣውን ዕድል መጠቀም የምንችለው የሚመጡ አደጋዎችን በአግባቡ መከላከል ስንችል ነው ይላሉ።
ሀገራዊ የዲጂታል ሽግግር ለማረጋገጥ ሁልጊዜም የተቋማት የሳይበር ደህንነት ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል።
የሳይበር ጥቃት ሊያደርስ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና ለመከላከል የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ