Search

ከታዳሽ ኃይል 1.2 ቢሊዮን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የቻለችው ቻይና

ዓርብ ጥቅምት 21, 2018 9

ቻይና እ.አ.አ. በ2030 ከንፋስ እና ከፀሐይ ኃይል 1.2 ቢሊዮን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የያዘችውን ግብ ከወዲሁ አሳክታለች።
ባለፈው ዓመት ቻይና ለታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት ያወጣችው 625 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም በአጠቃላይ ዓለም ለታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት ከሚያወጣው አንድ ሶስተኛውን ይሸፍናል።
በአሁኑ ወቅት በቻይና በአንድ ሰዓት ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውለው ሶስት ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ አንዱ ኪሎ ዋት ከታዳሽ ኃይል የሚገኝ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ቻይና ከንፋስ እና ከፀሐይ ኃይል የሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይልን ወደ ጎረቤት ሀገራት እየላከች ነው።
በአጠቃላይም ሀገሪቷ በታዳሽ ኃይል አማካኝነት 4.1 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እንደቻለች ተመላክቷል።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ