ኃያላን ሀገራት በሕዋ ላይ የበላይ ለመሆን የሚያደርጉት ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
ቻይናም ለመጀመሪያ ጊዜ በጠፈር ላይ በአጥቢ እንስሳት ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉ ጠፈርተኞችን እና ለጥናቱ የሚያስፈልጉ አይጦችን የያዘ ቡድን ወደ ዓለም አቀፉ የሕዋ የምርምር ጣቢያ መላኳን አስታውቃለች።
ጠፈርተኞቹ የስድስት ወራት ተልዕኮ እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በቆይታቸው የተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ያከናውናሉ መባሉን የሀገሪቷ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ምን አልባትም ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ከመሬት ውጪ ለረጅም ጊዜ መኖር ይችላሉ? የሚለውን ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ፍንጭ ለማግኘት እየጣርኩ ነው የምትለው ቻይና የተለያዩ ምርምሮችን በማድረግ ላይ ትገኛለች።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ