Search

ለሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያወጡ ያሉት ግዙፍ የቴክኖጂ ኩባንያዎች

ማክሰኞ ጥቅምት 25, 2018 51

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) በቅርብ ጊዜ የተጀመረ ቢሆንም አስፈላጊነቱ እና ተፅዕኖው ዓለምን በማዳረስ ረገድ ከፍተኛ ነው።
በርካቶችም በዚህ መፃኢ ጊዜን ይበይናል በተባለው ዘርፍ ቀዳሚ ለመሆን በውድድር መንፈስ እየሠሩበት ይገኛሉ።
ከኦፕን ኤ.አይ እስከ ሜታ ያሉ ታላላቆቹ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን እየመደቡ ነው።
ኦፕን ኤ.አይ እና አማዞን በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ የኤንቪዲያ ‘ፕሮሴሰር’ ተጠቃሚዎች አገልግሎትን ለማሻሻል 38 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የረጅም ጊዜ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሠረት ኦፕን ኤ.አይ እ.አ.አ እስከ 2026 መገባደጃ የአማዞንን የድረ-ገፅ አገልግሎቶችን (AWS) የሚጠቀም ይሆናል፤ ስምምነቱ ሊራዘም እንደሚችልም ተገልጿል።
ብላክሮክ፣ ማይክሮሶፍት እና ኤንቪዲያ የሚገኙበት የኢንቨስትመንት ቡድን በአሜሪካ የሚገኘውን እና ከዓለማችን ግዙፍ የዳታ ማዕከላት አንዱ የሆነውን ‘አላይንድ ዴታ ሴንተርስ’ በ40 ቢሊዮን ዶላር ሊገዛ መሆኑ ታውቋል። ማዕከሉ ወደ 80 የሚጠጉ አገልግሎቶችን በውስጡ ያካተተ ነው ተብሏል።
ኦፕን ኤ.አይ የመጀመሪያዎቹን የቤት ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ፕሮሰሰሮችን ለማምረት ከብሮድኮም ጋር ጥምረት ፈጥሯል።
‘አድቫንስድ ማይክሮ ዲቫይስዝ (AMD)’ አዳዲስ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ቺፖችን ለኦፕን ኤ.አይ ለማቅረብ የተስማማ ሲሆን፤ በስምምነቱ መሠረት ኦፕን.ኤ.አይ የ‘AMD’ን እስከ 10 በመቶ ድርሻ መግዛት ይችላል።
ሜታ ከኦራክል ጋር የ20 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የ‘ክላውድ’ አገልግሎት አቅርቦት ስምምነት ለመፈራረም እየተነጋገረ ያለ ሲሆን፣ ይህም ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋም ፈጣን ተደራሽነትን ለማስጠበቅ ያለውን ጥረት አጉልቶ እንደሚያሳይ የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል።
በለሚ ታደሰ