በቻይና በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ፣ የጄትሮብ ቡድን በመባል የሚታወቅ የተመራማሪዎች ቡድን በጀርባ ላይ የሚታዘል እንዲሁም በክንድ ላይ የሚጠለቁ ሞተሮች ያሉት መብረሪያ መሣሪያን ይፋ አድርጓል።
መሣሪያው በአምስት ሞተሮች የሚንቀሳቀስ ሲሆን አብራሪው አቅጣጫውን እና ከፍታውን በክንድ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጣጠር ያስችለዋል።
ሰዎች መሣሪያውን በመጠቀም አየር ላይ ሆነው አካባቢያቸውን እየተመለከቱ ከመሬት ከፍ ብለው መብረር ይችላሉ ተብሏል።
በቅርብ ጊዜ በተደረገ ሙከራ አንድ ሰው በመሣሪያው ታግዞ በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል።
በሴራን ታደሰ
#EBC #EBCDOTSTREAM #jetpoweredbackpack #China