Search

ቱርኪዬ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም የተሠራ ፈጣን ባቡር ሥራ ልታስጀምር ነው

ረቡዕ ጥቅምት 26, 2018 30

ለባቡር እና ለባሕር ትራንስፖርት ዘርፎች ትኩረት በመስጠት እየሠራች ያለችው ቱርኪዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የተሠራ እና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ባቡር እአአ በ2026 ወደ ሥራ እንደምታስገባ አስታውቃለች።
ፈጣን ባቡሩ በሰዓት 225 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም ያለው ነው።
ቱርኪዬ ከዚህ ቀደም ለባቡር እና ለባሕር ትራንስፖርት የሚወጣውን የሀገር ሀብት በራስ አቅም ለመተካት ያለሙ ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነች ነው።
በዚሁ መሠረት ፈጣን የኤሌክትሪክ ባቡሮችን እና ሀዲዶችን በራስ አቅም ማምረት ጀምራለች።
በቱርኪዬ ሳካሪያ ግዛት የሚገኘው እና ቱራሳስ የተባለው የፈጣን ኤሌክትሪክ ባቡሮች ፋብሪካ አሁን ላይ በርካታ የባቡር አካላትን በማምረት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በዚህም ሀገሪቱ በየዓመቱ ለዘርፉ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ማስቀረት መቻሉን የዘገበው አናዶሉ ነው።
በባቡር ዲዛይኖች እና ሲስተሞች ላይ በተከናወኑ የምርምር ሥራዎች መሠረት ቱርኪዬ አሁን ላይ ከዓለማችን የፈጣን ባቡር ባለቤቶች መካከል አንዷ ለመሆን ተቃርባለች።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ