Search

ትራፊኩ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል

ረቡዕ ጥቅምት 26, 2018 37

በቻይና ዤጂያንግ ግዛት፣ ቶንግሺያንግ ከተማ አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ሮቦት በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

የ1 ሜትር ከ80 ሳ.ሜ ቁመት ያለው ትራፊኩ ሮቦት ዛሬ በይፋ ሥራውን መጀመሩን ተከትሎ የቶንግሺያንግ ከተማን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ላይ ይገኛል።

አቅጣጫዎችን እና የተለያዩ የመንገድ ትራፊክ ምልክቶችን እንዲረዳ ተደርጎ የተፈበረከው ሮቦቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በተገቢው መንገድ በመረዳት ሥራውን በአግባቡ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

#ebcdotstream #china #robottrafficofficer