ወላጆች የልጆቻቸውን እንቅስቃሴ መከታተል የሚችሉበት ሲም ካርድ ይፋ መደረጉን የሩሲያ ዲጂታል ልማት፣ ኮሙኒኬሽን እና መገናኛ ብዙኃን ሚኒስትር ማክሱት ሻዳዬቭ አስታውቀዋል።
ሲም ካርዱ የሕፃናት ደኅንነትን ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀው ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ሲም ካርዱ ከ14 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች ተገቢ ያልሆኑ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ይዘቶችን እና የማይመከሩ ድረ-ገጾችን ማየት እንዳይችሉ የሚገድብ እንደሆነም ተገልጿል።
ወላጆች ሲም ካርዱ የሚልክላቸውን መረጃ ተጠቅመው ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንደሚችሉም ተመላክቷል።
ሲም ካርዱ የሚሰጠው በወላጆች ፈቃድ ብቻ መሆኑን የዘገበው ቻይና ኒውስ ነው።
ይሁንና ወላጆች የልጆቻቸውን የእንቅስቃሴ መረጃ የሚከታተል ሌላ አካል ከፈለጉ በራሳቸው ፈቃድ ኃላፊነቱን መስጠት ይችላሉ ተብሏል።
በሔለን ተስፋዬ