Search

ከፍተኛ ሙቀትን በመቋቋም ለእሳት አደጋ ሰራተኞች መረጃ የሚያቀብለው ሮቦት

ቅዳሜ ጥቅምት 29, 2018 38

ከባድ የእሳት አደጋ ሲከሰት ከውስጥ ሆኖ መረጃ የሚያቀብል ወይም አቅጣጫ የሚጠቁም አካል ማግኘት የማይታሰብ ነው።

የእሳት አደጋ በሚያጋጥምበት ወቅት የአደጋ ሰራተኞች ወደተቃጠለው ቦታ በድፍረት መግባት፣ ጭስ እና የማይታወቅ ነገርን የመጋፈጥ ግዴታ ይኖርባቸዋል።

ታዲያ በቴክሳስ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህን ችግር ለመፍታት ከ1ሺ ዲግሪ ፋራናይት በላይ የሙቀት መጠንን መቋቋም የሚችል ሮቦት አስተዋውቀዋል።

"ፋየር ቦት" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሮቦቱ፤ 300 ፓውንድ የሚመዝን እና 48 ኢንች ርዝማኔ ያለው ሮቦት ሲሆን ለእሳት አደጋ ሰራተኞች መረጃ ለመሰብሰብ ወደተቃጠለው ቦታ መግባት የሚችል ነው ተብሏል።

ሮቦቱ በከባድ የእሳት ቃጠሎ ውስጥ ዘልቆ ከገባ በኋላም ለእሳት አደጋ ሰራተኞች  የአደጋውን ሁኔታ እንዲረዱ እና መረጃ እንዲያገኙ አንደሚያግዝም ተጠቁሟል።

የ"ፋየር ቦት" ሃሳብ የመነጨው ከቴክሳስ ተማሪዎች አንዱ በሆነው ኒኪል ታኩር ነበር።

ሃሳቡንም ያመነጨው ከ13 ዓመታት ገደማ በፊት የ 10 ዓመት ልጅ እያለ በሂዩስተን በተከሰተ አሳዛኝ የእሳት አደጋ አምስት የእሳት አደጋ ተከላካዮችን ከሞቱ በኋላ ሲሆን ሁለቱንም በግል ያውቃቸው እንደነበር ለሲኤንኤን ተናግሯል።

ታኩር "ፋየር ቦት በአደገኛ አካባቢዎች ውስጥ መረጃ  ይሰጣል፣ የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎችን ከጉዳት ይጠብቃል" ብሏል።

ከማይዝግ ብረት፣ ቱንግስተን እና ቲታኒየም ከተሰኙ ንጥረ ነገሮች የተሰራው ሮቦቱ፤ ከፍተኛ ሙቀትን፣ ኬሚካሎችን እና ናዳን ለመቋቋም የተገነባ መሆኑ ተጠቅሷል።

በሴራን ታደሰ

#EBC #EBCDOTSTREAM #Robot #Firefighters