በዓለማችን ላይ በአሁኑ ሰዓት ከአምስተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5ጂ) ወደ ስድስተኛው ትውልድ (6ጂ) ለመሸጋገር በርካታ ምርምሮች በመደረግ ላይ ናቸው።
በፈረንጆቹ 2030 ምርምሮች ወደ መሬት ወርደው የ6ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይሁን እንጂ ከዚህ ጊዜ ቀድሞ የፈጠራው ባለቤት ለመሆን ሀገራት ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
ከአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ በ100 እጥፍ ፍጥነት እንደሚበልጥ የተነገረለት የ6ኛው ትውልድ ኔትወርክ አንድ ቴራ ባይት ፋይል ለማውረድ በቀደመው ጊዜ 13 ደቂቃ ይፈጅ የነበረውን ጊዜ ወደ 8 ሰከንድ የሚያሳጥር ነው፡፡
ቻይና አሁን ባለው የምርምር ሁኔታ በ6ጂ ኔትወርክ ፈጠራ ላይ የሚታይ እድገት በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡
እንደቻይና ሳይንስ ዘገባ ሀገሪቱ በሲስተም ዲዛይን እና የኔትወርክ አርክቴክቸርን ጨምሮ ከ300 በላይ ቁልፍ የ6ጂ ኔትወርክ ምርምር እንዳላት አስታውቃለች።
በዚህ ብቻ ያላቆመው የቻይና የሙከራ ሂደት የ6ጂ የሙከራ ሳታላይት ማበልጸግ መጀመሯ አንድ እርምጃ መቅደሟን አመላካች ነው ተብሏል።
አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ጃፓን እና የአውሮፓ ሀገራትም በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መድበው በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ማን ቀድሞ የቴክኖሎጂው ባለቤት ይሆናል የሚለው የሚጠበቅ ነው።
በቦታዎች ተወስኖ አገልግሎት የሚሰጠውን የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ አዲሱ የስድስተኛ ትውልድ ኔትወርክ ያለገደብ እንዲሰራም የሚያደርግ ነው፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#Ebc #Ebcdotstream #6GNetwork