5ኛው የአፍሪካ አቪዬሽን ማሰልጠኛዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምራል።
ጉባዔው የአፍሪካን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ምቹ፣ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ለማድረግ ያለመ ነው።
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ ደንጌ ቦሩ ጉባዔውን ሲከፍቱ እንዳሉት፥ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ለኢኮኖሚው የሚያበረክተው ድርሻ የላቀ በመሆኑ የሰው ኃይል ልማት ላይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል።

ንግድን በማቀላጠፍ፣ የቱሪዝም ዘርፉን በመደገፍ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማጎልበት ረገድም የዘርፉ አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ቀጣይነት ላለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ ዘርፉን ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑም ነው የተገለጸው።
የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በየዓመቱ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ለኢንዱስትሪው እያቀረበ ይገኛል።
እስከ ነገ የሚዘልቀው 5ኛው የአፍሪካ አቪዬሽን ጠቅላላ ጉባዔ እንደ አህጉር በዘርፉ በተለይ በመሠረተ ልማት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት በሚያስችሉ ሥራዎችም ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።
በአልጋነሽ ተካ
#ebcdotstream #aviation #Africa #Ethiopia #AddisAbaba