Search

ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ሆትስፐር አቻ ተለያየ

እሑድ ጥር 24, 2018 107

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ከቶተንሀም ሆትስፐር ባደረገው ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡
ሲቲ ራያን ቼርኪ እና አንቶኒዮ ሴሜኒዮ ባስቆጠሯቸው ግቦች እየመራ ለእረፍት ቢወጣም ማሸነፍ አልቻለም፡፡
በ2ኛው ግማሽ ዶሚኒክ ሶላንኬ የቶተንሀምን ግቦች አስቆጥሯል፡፡
ማንችስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት የሚያጠብበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
ከባለፉት ስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፈው ማንችስተር ሲቲ በ47 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርሰናል በስድስት ነጥብ ከፍ ብሎ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡
 
በአንተነህ ሲሳይ