በቻይና በሀገር በቀል ቴክኖሎጂ የተገነባው "ሁዋሎንግ ዋን" (Hualong One) በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኝ የሶስተኛ ትውልድ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት 41 የሁዋሎንግ ዋን የሃይል ማመንጫ ዩኒቶች በስራ ላይ ወይም በግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የቻይና ሳይንስ መረጃ ያመለክታል።
አንድ የኋሎንግ ዋን ዩኒት ብቻ በዓመት 10 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት (kWh) የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው።
ይህ ቴክኖሎጂ በዓመት 8.16 ሚሊዮን ቶን የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ትልቅ ሚና የሚጫወት ሆኗል።
ይህም ብቻ ሳይሆን በየዓመቱ ከ3 ሚሊዮን ቶን በላይ የድንጋይ ከሰል አጠቃቀምን የሚያስቀር መሆኑ በከባቢ ላይ የሚደርስን ጉዳትም በመቀነስ አስተዋጻኦው የጎላ ነው።
ቻይና በአውሮፓውያኑ 2030 የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎቿን ቁጥር ከ100 በላይ ለማድረስ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች።
በአውሮፓውያንኑ 2025 ማብቂያ ላይ ቻይና በስራ ላይ ያሉ፣ በመገንባት ላይ ያሉ ወይም ግንባታቸው የጸደቀ 112 የኒውክሌር ኃይል ዩኒቶች ነበሯት።
ከአውሮፓውያኑ 2026 እስከ 2030 በሚቂየው የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ዘመን የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ የኒውክሌር ኃይል ዩኒቶች ቁጥር ከ100 በላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ