Search

ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኬንያ አቻቸው ጋር ተወያዩ

እሑድ ጥር 24, 2018 70

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኬንያው የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ፣ የውጭ እና ዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ከሆኑት ሙሳሊያ ሙዳቫዲ (ዶ/ር) ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ።
ሚኒስትሮቹ ረዥም ዘመን ያስቆጠረውን እና በጊዜ የተፈተነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም በኢኮኖሚ ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።
ሁለቱ ወገኖች ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውሕደትን በማጠናከር በአፍሪካ ቀንድ ልማትን ለማስፋፋት፣ ሰላም እና ደኀንነትን ለማጠናከር የበለጠ ተቀራርበው ለመሥራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል።