ዛሬ በባህር ዳር ከተማ የሚገኘውን አማጋ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን መጎብኘታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ፋብሪካው በቅርቡ ወደ ሥራ መግባቱን በማኅበራዊ የትስስር ገፅ አስፍረው፤ የፋብሪካው ተከላ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅም በዋናነት ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ፣ የሶፋ ልብስ፣ መጋረጃ፣ የአንሶላ ጨርቅ፣ ጂንስ እና ሌሎች የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች በተለያዩ ዲዛይኖችና ልኬት ማምረት ያስችለዋል ብለዋል።
ጥራት ያላቸው ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ እና በቀጥታ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት የሚጥሩ ፋብሪካዎች ሀገራዊ አበርክቷቸው ቀላል የሚባል አይደለም ሲሉም ገልጸዋል።