Search

ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን በትብብር ለመሥራት መግባባት ላይ ደረሱ

ሰኞ ጥር 25, 2018 129

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (/ር) ከሳውዲ አረቢያ አቻቸው ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሃን አል ሳዑድ ጋር በሪያድ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በሀገራቱ መካከል ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በፖለቲካ ኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ይበልጥ በማጠናከር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

በጋራ የቀጣናዊ ሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያም በስፋት የተወያዩ ሲሆን፤ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን በትብብር ለመሥራት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

በውይይቱ በሳውዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (/ር)፣ የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና ፓሲፊክ ሀገራት ዳይሬክቶሬት ጄነራል አምባሳደር ደዋኖ ከድር እና ሌሎች ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

#Ethiopia #SaudiArabia #Diplomacy #ForeignRelations #HornOfAfrica #EthiopianBroadcastingCorporation