በመደመር መንግሥት የአመራር ስልት የዜሮ ግቦችን በመተግበር የኢትዮጵያን ብልጽግና ልናረጋግጥ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት "በመደመር ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል ርዕስ ለብልፅግና አመራሮች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው፡፡
በማብራሪያቸው የማንሰራራት ጉዟችን በብልጽግና ላይ እንዲያርፍ ከዞን እና ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አመራሮች የዜሮ ግቦችን ሊተገብሩ ይገባል በማለት ተልዕኮውን አውርደዋል፡፡
በዚህም መለመንን የሚያለማምደውን ተረጂነት ዜሮ ማድረግ፣ የማይታረስ መሬት ወደ ዜሮ እንዲወርድ መትጋት እንዲሁም ከመኖሪያ እና ከሰፈሩበት አካባቢ የሚፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርን ዜሮ ለማድረስ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
እንዲሁም የኢኮኖሚ ሰርሳሪ የሆነው የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴን ዜሮ በማድረግ ማሽመድመድ፣ ሌብነትና አጭበርባሪነትን ዜሮ ማድረግ የአመራሮች ግብ ሊሆን እንደሚገባ አስቀምጠዋል፡፡
በአፎሚያ ክበበው