Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በይፋ አስጀመሩ

ሰኞ ሰኔ 08, 2018 416

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በዚህ ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ አስቀምጠን፣ ከፍ ወደ አደረግነው 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል።

‎ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጭው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራዎን ያኑሩ ሲሉም ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: