ሚዲያ ካለው ቁልፍ ሚና እና ከተጣለበት ለእሴት የመገዛት ኃላፊነት በመነሳት አራተኛው የመንግሥት አካል ተደርጎ ይወሰዳል።
ሚዲያ ማህበረሰብን ማሳወቅ እና መገንባት፣ ግልፀኝነት እና ተዓማኒነት እንዲፈጠር መሥራት ከፍ ሲልም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠቅ ላይ ትልቅ ድርሻ አለው።
አሁን ላይ ከመደበኛ የስርጭት ጣቢያዎች ባልተናነሰ በዲጂታል ሚዲያ ላይ ባሉ ተደራሽነቶችም ቢሆን እነዚህ ኃላፊነቶች ተጠናክረው የቀጠሉ ናቸው።

እንደ ኢትዮጵያ ሕልውናው በብሔራዊ ጥቅም መከበር ላይ ለተመሠረተ ሀገር ደግሞ የሚዲያ ሚና አንደምታው ትልቅ ስለመሆኑ ጋዜጠኛ መሀመድ ሀሰን ይናገራል።
የሀገርን የወል ትርክት ያልፈተለ እና ለብሔራዊ ጥቅም መጠበቅ ያልሠራ ሚዲያ ሀገር የሌለው ሚዲያ ነው ሲል ሀሳቡን ገልጿል ጋዜጠኛ መሀመድ ከኢቲቪ ጋር በነበረው ቆይታ።
የስርጭት ጣቢዎችን በተለምዶ የዚህ ሀገር ሚዲያ እያልን በጎራ የምናስቀምጣቸው በዋናነት ለቆሙለት ሀገር እና ህዝብ ጥቅም መከበር ስለሚሰሩ መሆኑን ይናገራል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ዜጎች ማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ መፍጠር የሚችለውን ተፅዕኖ ተገንዝበው መሆን እንዳለበት ይገልፃሉ።
ዜጎች ማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የኢትዮጵያ ጥቅም በሚያስጠብቅ እና በሚያስከብር መልኩ እንዲጠቀሙ በማንቃት ረገድ ደግሞ መደበኛ (ባህላዊ) ሚዲያዎች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ነው ያሉት።
በአፎሚያ ክበበው
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #socialmedia