Search

ባቡር ጣቢያ ውስጥ ማየት የተሳናቸውን ሰዎች የሚመራው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ

ሰኞ ታኅሣሥ 06, 2018 73

በቻይና የሚገኘው የሸንዘን ሜትሮ የባቡር ጣቢያ ድርጅት ማየት ለተሳናቸው ደንበኞቹ ድጋፍ መስጠት የሚችል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ አዲስ የፈጠራ ሥራን ይፋ አድርጓል፡፡
ድርጅቱ ይፋ ያደረገው ቴክኖሎጂ ማየት የተሳናቸው ሰዎች በባቡር ጣቢያ ውስጥ ያለምንም ችግር እንዲንቀሳቀሱ እና ወደሚፈልጉት ቦታ እንዲጓዙ የሚረዳ መሆኑን ገልጿል።
በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለው ቴክኖሎጂው "በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚመራ ውሻ (AI Guide Dog) " የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፤ ካሜራ፣ የድምፅ መለያ እና ሌሎች ዘመናዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎችን አዋህዶ የያዘ ነው፡፡
ቴክኖሎጂው ለተጠቃሚዎቹ በመንገዳቸው የሚያጋጥማቸውን ነገር በድምፅ እየገለፀ ከግጭት በመጠበቅ አስተማማኝ ድጋፍ መስጠትም ይችላል ተብሏል፡፡
በአካባቢው ያለውን ድምፅና ምስል እንዲሁም እንቅፋት ያለበትን ቦታ በመለየትም መረጃውን ለተጠቃሚው ያስተላልፋል።
የባቡር ኩባንያው አዲስ ቴክኖሎጂ የተሳካ ሙከራ ማድረጉን ፒፕልስ ዴይሊ ቻይና ዘግቧል፡፡
 
በላሉ ኢታላ