በዓለም ላይ ያሉ 8 ቢሊዮን ሰዎች የየራሳቸው የጠረጴዛ ውይይቶች አሏቸው፤ ነገር ግን ዓለምን የማዳኑ ትልቁ የ COP32 ውይይት የሚጀምረው የቡና መገኛ ምድር ከሆኑት ከአቦል፣ ቶና እና በረካ መድረኮች ነው።
ቡና ለአገራችን የባህልና የትስስር መገለጫ ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ የሚያስተሳስር ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታችን ነው።
ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተው ይህ መዓዛ ያለው የትስስር ጥበብ ዛሬ ላይ ለአየር ንብረት ለውጥ ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመፈለግ በሚደረገው ዓለም አቀፋዊ ውይይት ላይ ትልቅ መንፈሳዊና ባህላዊ መነቃቃትን ይፈጥራል።
ከአቦል እስከ COP32 በሚዘልቀው በዚህ ታሪካዊ ጉዞ ኢትዮጵያ ተፈጥሮን በመንከባከብና በአረንጓዴ ልማት ዓለምን የምታስተሳስርበትን አኩሪ ሚናዋን በላቀ ደረጃ ትወጣለች።
ከቡና መገኛ ምድር ወደ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሔ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: