Search

በባለብዙ ወገን ዓለም ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው የሩሲያ አፍሪካ ታሪካዊ አጋርነት

ማክሰኞ ጥቅምት 17, 2019 54

በሩሲያ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ተቋም ዋና የምርምር ባልደረባ ዲሚትሪ ትሬኒን ጥናታዊ ትንተና ላይ በመመስረት የሩሲያ እና የአፍሪካ ግንኙነት እያደገ መሆኑን መመልከት ይቻላል።

በዚህ ጥናት መሰረት ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውስጥ እያደገ የመጣበትን እና ወደ ላቀ የትብብር ደረጃ እየሸጋገረ ያለበትን ሁኔታ በጥልቀት መመልከት ይቻላል።

በሶቭየት ሕብረት ዘመን የነበረው ጥልቅ ትብብር ዛሬ ላይ በዘመናዊ ዓለም አቀፍ ትስስርና በባለብዙ ወገን ዓለም ቅደም ተከተል ውስጥ እንደገና እየተጠናከረ መጥቷል።

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ስትሰራ እንደ ቀድሞው ቅኝ ገዢዎች አገሮችን ለመበዝበዝ ሳይሆን አፍሪካን የእኩልነት ድምፅ አላት ብላ በማመን ከዓለም አቀፍ አብላጫ (Global Majority) ጋር በመተባበር ላይ ትገኛለች።

በሃይል፣ በምግብ ዋስትና፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጸጥታና ደህንነት መስኮች ሩሲያ ለአፍሪካ አገራት አስተማማኝ አጋር መሆን ችላለች።

በተለይም እንደ ማሊ፣ ኒጀር፣ ቡርኪና ፋሶ እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባሉ አገራት ውስጥ የደህንነት ስጋቶችን በመመከት እና የሉዓላዊነትን ከፍ አድርጎ በመያዝ ረገድ የአፍሪካ ኮርፕስ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

ከዚህም ባለፈ እንደ ኤቦላ እና ኮቪድ-19 ያሉ ገዳይ ወረርሽኞችን ለመከላከል የተደረጉ የሳይንስ ምርምሮች እና እንደ ቬክተር (Vector) እና ስፑትኒክ ቪ (Sputnik V) ያሉ ክትባቶች ማስተዋወቅ የሁለቱን አህጉራት ትብብር ይበልጥ አጠናክሮታል።

በዚህ ሁሉ አህጉራዊ ትስስር ውስጥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ነው።

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በረጅም ታሪክ ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ያላት ሲሆን፤ ዛሬ ላይ ደግሞ ከሩሲያ፣ ከግብፅ እና ከደቡብ አፍሪካ ጋር በመሆን የብሪክስ (BRICS) ሙሉ አባላት በመሆን በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የኢኮኖሚ መድረኮች ላይ የጋራ ጽኑ አቋማቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።

የብሪክስ ማዕቀፍ አገራት ሉዓላዊነታቸውን የሚያከብር፣ አንዳችም ርዕዮተ-ዓለምን በሃይል የማይጫን እና በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር እንዲኖር አብረው እየሰሩ ናቸው።

በሌላ በኩል 35,000 የሚጠጉ ወጣት አፍሪካውያን በሞስኮ በሚገኘው የፓትሪስ ሉሙባ ስም በተሰየመው የሕዝቦች ወዳጅነት ዩኒቨርሲቲን (Peoples’ Friendship University) ጨምሮ በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች በሕክምና፣ በኢነርጂ እና በምህንድስና ዘርፎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ናቸው። ይህም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።

በሞስኮ በሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ አማካኝነት የኢትዮጵያ እና አፍሪካ ከሩሲያ ጋር ያላቸው ሁለገብ አጋርነት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

በጌቱ ላቀው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: