Search

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

እሑድ ጥቅምት 22, 2019 165

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በይፋ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

የደብረ ብርሃን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በከተማዋ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል። ማዕከሉ በርካታ ተቋማትን ያቀፈና በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር በአንድ ጊዜ መስጠት የሚያስችል አቅም ያለው ነው።

በአማራ ክልል ዘመናዊና የተቀናጀ አሰራርን በመዘርጋት የህዝብን የእለት ተእለት ፍላጎት በብቃት ለማሟላት የሚያስችሉ መሰል «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት በስፋት እየተገነቡ ለአገልግሎት እየበቁ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

በዛሬው የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: