በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ዘላቂ የዲጂታል እመርታ እንዲመዘገብ ይሠራል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዲጂታል ትራስፎርሜሽን ብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ኢትዮጵያ የማደግ ፍላጎትና አቅም ያላት ሀገር መሆኗን ያወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ዲጂታል መርሐ ግብር ፈጠራ፣ ፍጥነትና እመርታን በማምጣት የማደግ ፍላጎታችንን ከአቅማችን ጋር እንዲናበብ እያደረገ ነው ብለዋል።

የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማስፋት ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች እንደተመዘገቡበት ገልጸው፤ በመንግሥት አሠራር፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ተደራሽነት ላይም ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን አክለዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዛሬ ይፋ መሆኑን ተከትሎም በቀጣይ አምስት ዓመታት በሀገራችን በሁሉም መስኮች ዘላቂ የዲጂታል እመርታ እንዲመዘገብ እንደሚሠራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #DigitalEthiopia #DigitalEthiopia2030 #PMOEthiopia