Search

በታሪካዊው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ተዘጋጅተናል፦ የወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 51

ነገ በአንድ ጀምበር በሀገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የነገው ሀገራዊ የጋራ አጀንዳችን ችግኝ መትከል ብቻ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ፣ በማለዳው ከቤተሰቦቻችን ጋር ሆነን በተዘጋጁት የችግኝ ተከላ ሳይቶች በመገኘት ዐሻራችንን ለማኖር ተዘጋጅተናል ሲሉ በከፍተኛ ተነሳሽነት ገልጸዋል።

አረንጓዴ ዐሻራን ማኖር ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ መሠረት መጣል መሆኑን የጠቀሱት ነዋሪዎች፤ የከተማዋ ሕዝብ በነገው ዕለት በነቂስ ወጥቶ በዚህ ታሪካዊ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ተሳትፏችን ችግኞችን በመትከል ብቻ የሚያበቃ አይደለም፤ የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብም ተዘጋጅተናል ነው ያሉት።

ለነገው መርሐ ግብር በከተማዋ የጉድጓድ ቁፋሮን ጨምሮ የተከላ ቦታዎች የማዘጋጀት፣ ችግኞችን የማቅረብ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ተደርገዋል።

በትዕግስቱ ቡቼ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: