በአፋር ክልል 52 አካባቢዎች ተለይተው ለነገው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዝግጁ ተደርገዋል።
የጉድጓድ ቁፋሮ እና የሚተከሉ ችግኞች ማጓጓዝን ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራው ተጠናቅቋል።
በዕለቱ የጥላ ዛፎች እንዲሁም ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች ይተከላሉ።
የሰመራ ከተማዋ ነዋሪዎችና አመራሮች፣ አረንጓዴ ዐሻራ የአፋርን በረሃማ አካባቢዎች በፍጥነት በመቀየር መሬቷ ለምለም መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል።
ለነገው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዝግጁ መሆናቸውንም ነዋሪዎቹና አመራሮቹ ገልጸዋል።
በብሩክታዊት ተገኝ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: