Search

በሲዳማ ክልል ለነገው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቅቋል

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 50

በሲዳማ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ለነገው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቅቋል።

የዘንድሮው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በክልሉ 4 ሄክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ ለማከናወን ታቅዷል

4 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ በተመረጡ ቦታዎች የጉድጓድ ቁፋሮ እና ችግኝ ማጓጓዝን ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራው መጠናቀቁን የክልሉ እርሻ፣ ተፈጥሮ ሀብት እና ደን ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አበባየሁ በየነ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

ለተከላ ከተመረጡ ቦታዎች አንዱ የሆነው በዳሌ ወረዳ የጎሎላ ተፋሰስ አካባቢ አርሶ አደሮች በበኩላቸው፣ ነገ ከማለዳው ጀምሮ በአንድ ጀምበር መርሐ ግብሩ በንቃት በመሳተፍ ዐሻራቸውን ለማኖር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄደው ተከላ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በሚካኤል ገዙ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: