በመላው ሀገራችን 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው ታሪካዊ ሀገራዊ መርሐ ግብር መሠረት በሐረሪ ክልል በነገው ዕለት ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ሙሉ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነስሩ አህመድ እንደገለጹት መርሐ ግብሩን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ ሥራዎች ተከናውነዋል።
ለዚህም የተለያዩ የችግኝ ዝርያዎች ተዘጋጅተው ወደ ተከላ ቦታዎች የተጓጓዙ ሲሆን፣ የጉድጓድ ቁፋሮ ሥራውም ተጠናቅቋል።
የችግኝ ተከላው በጥናት በተለዩ 14 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በይፋ የሚከናወን ሲሆን፤ ቦታዎቹ ችግኞቹ በአግባቡ እንዲጸድቁ እና ለክትትል ሥራ እንዲመቹ በጥንቃቄ የተመረጡ ናቸው።
በነገው ዕለት በሚካሄደው በዚህ የአንድ ጀምበር መርሐ ግብር ላይ ከ20 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: