Search

አዲስ አበባ ችግኞችን ጭምር በመለየት ለነገው የአንድ ጀምበር ተከላ ተዘጋጅታለች

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 69

ነገ ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ችግኞች ተለይተው ለተከላ ተዘጋጅተዋል።

በከተማዋ ለነገው መርሐ ግብር የሚያስፈልጉ ችግኞችን የማዘጋጀት፣ የመለየትና የማጓጓዝ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ተመልክቷል።

በየተከላ ሳይቱ ለአካባቢው አየር ንብረትና አፈር ተስማሚ የሆኑ የጥላና የፍራፍሬና እንዲሁም ሀገር በቀል ችግኞች ተለይተው ለተከላ ዝግጁ ሆነዋል።

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው መርሐ ግብር የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለመሳተፍ በከፍተኛ ተነሳሽነት ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: