የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ የፈረንጆቹ 2026 የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ፣ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ አዲሱ የኅብረቱ ሊቀመንበር መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።
አዲሱ ሊቀመንበር ኃላፊነቱን የተረከቡት የኅብረቱ የ2025 ሊቀመንበር ከነበሩት የአንጎላ ፕሬዚዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ ሲሆን፣ ርክክቡን ተከትሎም በይፋ ሥራቸውን ጀምረዋል።