Search

ከመጪው ትውልድ የተዋሰናት ሀገር፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትውልድ ግንባታ ፍልስፍና እና ተጨባጭ ስኬቶች

ማክሰኞ መጋቢት 22, 2018 92

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በተለያዩ መድረኮች እና በመጽሐፎቻቸው በተደጋጋሚ የሚያነሱት አንድ መሰረታዊ ብሂል አላቸው፤ "ሀገር ከአባቶቻችን የወረስናት ብቻ ሳትሆን፣ ከመጪው ትውልድ የተዋስናትም ጭምር ናት" የሚለው መርሕ መንግሥታቸው ለሚከተለው የትውልድ ግንባታ ፖሊሲ ዋነኛ የማዕዘን ድንጋይ ነው፡፡

ይህ አባባል ሀገርን እንደ ጥንታዊ ቅርስ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ አስውቦ እናበልጽጎ ማስረከብ የሚገባ ታሪካዊ ዕዳ አድርጎ የሚቆጠር ጥልቅ ፍልስፍና ነው፡፡

ባለፉት ስምንት ዓመታት የተመዘገቡት ሀገራዊ ውጤቶችም ይህንን "ውሰት" በላቀ ደረጃ ለመመለስ የተደረጉ ስልታዊ ኢንቨስትመንቶች መሆናቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

የትውልድ ግንባታው መሠረት የሚጣለው በሕፃናት ላይ መሆኑን የተረዳው መንግሥት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አማካኝነት የጀመረው የቀዳማይ ልጅነት መርሐ ግብር ለነገው ዜጋ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ብቃት ትልቅ ዋስትና ሆኗል፡፡

12 ሺህ በላይ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን ለመገንባት የወጣው መመሪያ እና በተግባር የታዩት ውጤቶች ከተማዋን ለሕፃናት ምቹ እያደረጓት ነው፡፡

የሕፃናት መጫወቻ እና ማዘውተሪያዎች በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ከተሞች ቀጥሏል፡፡ ከዚህም በላቀ ሁኔታ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ  ብቻ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1 ነጥብ 6 ሚለዮን በላይ ተማሪዎች የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚሲሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የትምህርት ቤት ምገባ በትውልድ ግንባታ ሂደት ውስጥ ረሃብ ለዕውቀት እንቅፋት እንዳይሆን የተወሰደ ታሪካዊ እርምጃ ነው፡፡ ይህ ጥረት ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ እያገኙ በትምህርታቸው እንዲገፉ በማድረግ ለነገው አምራች ኃይል ጤናማ መሠረት ጥሏል፡፡

ከአካላዊ ግንባታ ጎን ለጎን የትውልድ ግንባታው ሌላኛው ምሰሶ የአእምሮ ማዕድ ነው፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የዕውቀት ፋና ተደርጎ የሚወሰደው የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በቀን እስከ 10 ሺህ በላይ አንባቢዎችን እያስተናገደ የንባብ ባሕልን እየቀየረ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ወጣቱ ትውልድ ከተዛቡ ትርክቶች ወጥቶ በምክንያት እና በሳይንስ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ እንዲኖረው በሩን ከፍቷል፡፡

5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶችን በዲጂታል ዕውቀት በማስታጠቅ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ እንድትሆን እና የውጭ ምንዛሬ ገቢዋን እንድታሳድግ የሚያስችል ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ለወደፊቱ ትውልድ የሚተላለፈው ሀብት በቴክኖሎጂ እና በዕውቀት ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለነገው ትውልድ የምትመች እና የአየር ንብረት ለውጥን የተቋቋመች ሀገር ለማስረከብ የተጀመረው ሁለንተናዊ ጉዞ አካል ነው፡፡

በተቋማዊ ደረጃም የኢትዮጵያ ስታርትአፕ አዋጅ ቁጥር 1396/2017 መጽደቁ እና የልዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት (EGATE) መከፈቱ፣ የፈጠራ ሥራ ያላቸው ወጣቶች የራሳቸውን እና የሀገራቸውን ዕድል እንዲቀይሩ የሕግ እና የቦታ ከለላ ሰጥቷቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛ የሆነውን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ለመክፈት ያደረገችው ዝግጅትም በዘርፉ ቀዳሚ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ የተቀናጁ ተግባራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ከመጪው ትውልድ የተዋስናትን ሀገር አሳምረን እንመልስ በሚለው መርሐቸው መሠረት፣ ነገን ዛሬ ላይ እየገነቡ መሆናቸውን የሚያሳዩ የላቀ ስኬቶች ናቸው፡፡

ለሚ ታደሰ

#EthiopiaGenerationalBuilding #EarlyChildhoodDevelopment #EthioCoders #StartupEthiopia