Search

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የመስክ ስምሪት አድርጓል

እሑድ ግንቦት 23, 2018 39

ነገ ሰኞ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጥቂት ሰዓታት በቀሩበት በዚህ ወቅት፣ የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በመሬት ላይ ያለውን ሂደት በንቃት የመታዘብ ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

የቡድኑ የመስክ ታዛቢዎች በተመደቡባቸው ልዩ ልዩ ወረዳዎችና አካባቢዎች በመሰማራት፣ ከአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ አካላት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን በማድረግ ላይ ናቸው።

ታዛቢዎቹ በታችኛው መዋቅር ያለውን የቅድመ ምርጫ ዝግጅት፣ የሂደቱን ሁሉን አቀፍነት እና አጠቃላይ የድምፅ አሰጣጥ ከባቢ ሁኔታን በመገምገም፣ ለታዛቢ ቡድኑ አጠቃላይ ከምርጫ በኋላ ትንተና መሠረት የሚሆኑ እውነተኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ መሆናቸው ታውቋል።